Goh Betoch Bank

Bank of the Generation!                              SWIFT CODE: GOBTETAA

ለተከበራችሁ የጎህ ቤቶች ባንክ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ባንካችን ለሁሉም ባለአክሲዮኖች ለገዙት አክስዮኖች ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አዘጋጅቶ እየሰጠ ይገኛል። ነገር ግን በተለያየ ምክንያት አክሲዮን ሰርተፍኬቶቹን በአስቸኳይ የምትፈልጉ ካላችሁ ለአክሲዮን ክፍላችን ብታሳውቁ በቅድሚያ ተዘጋጅቶ መወሰድ ትችላላችሁ። እስካሁን የተዘጋጀላችሁና በፅሁፍ መልእክት ያሳወቅናችሁ ባለአክሲዮኖች መታወቂያችሁን በመያዝ ከአክሲዮን ክፍላችን መወሰድ ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያ የአክሲዮን ሰርትፊኬቶች የሚዘጋጁት አስፈላጊ ሰነዶች መሟላታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ስለሆነ በፋይላችሁ ላይ ያልተገኙ ሰነዶችን ከባንካችን አክሲዮን ክፍል በተጠየቃቹሁ ጊዜ አፋጣኝ ምላሽ እንድትሰጡን በትህትና እንጠይቃለን። በቀጣይ ተዘጋጅተው የሚጠናቀቁ ሰርተፍኬቶችን በፅሁፍ መልእክት የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ +251116686907 ስልክ ቁጥር ይጠቀሙ: