Goh Betoch Bank

Bank of the Generation!                              SWIFT CODE: GOBTETAA

ለተከበራችሁ የጎሕ ቤቶች ባንክ ባለአክሲዮኖች

በጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. የባለአክስዮኖች 1ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የባንኩ ካፒታል በብር ሁለት ቢሊዮን እንዲያድግ በተወሰነው መሰረት አብዛኞቻችሁ ባለአክስዮኖች የተመደበላችሁን አክሲዮን ጠቅላላ ዋጋ 1/4ኛ (25%) ወይም ከዚያ በላይ ከፍላችሁ አክሲዮናችሁን ማሳደጋችሁ ይታወቃል። በጠቅላላ ጉባዔው ዉሳኔ መሰረት በፈረማችሁት አክሲዮን ማሳደጊያ ውል ላይ እንደተገልጸው ቀሪው ክፍያ በየአመቱ ቢያንስ 1/3ኛ(25%) እየተከፈለ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡

ስለሆነም ባለአክሲዮኖች ያሳደጋችሁትን አክሲዮን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 2/3ኛ (75%) እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መከፈል ሲኖርበት ቀሪውም ክፍያ በሙሉ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተከፍሎ መጠናቀቅ እንዳለበት በአክብሮት እናሳዉቃልን።

ለበለጠ መረጃ 0116 68 72 52 በስራ ሰአት ይደውሉ፡፡