Goh Betoch Bank

ጎሕ ቤቶች ባንክ “ጎሕ ሞባይል አፕ” (Goh Mobile APP) የተሰኘ የሞባይልባንኪንግ መተግበሪያ አበልጽጎ አስመረቀ፡፡

ጎሕ ቤቶች ባንክ “ጎሕ ሞባይል አፕ” (Goh Mobile APP) የተሰኘ የሞባይልባንኪንግ መተግበሪያ አበልጽጎ አስመረቀ፡፡

ባንካችን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ልምድ ባላቸው ሰራተኞቹ በመታገዝ
ሁሉንም ቅርንጫፎች በኮር ባንኪንግ ሲስተም በማያያዝ ለደንበኞቹ ምቹና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት
በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ጎሕ ቤቶች ባንክ የቅርንጫፎቹን ቁጥር በማሳደግ ለደንበኞቹ ይበልጥ ቅርብና ተደራሽ በመሆን ምቾታቸውና ደህንነታቸውን የጠበቀ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ እየሰራ እንደሚገኝ የሚታወቅ
ሲሆን ከዚህ ቀደም በማንኛውም ስልክ ያለኢንተርኔት በአጭር ቁጥር ወይም USSD *916# አማካኝነት የባንክ አገልግሎት መጠቀም የሚያስችል አማራጭ ለደንበኞቹ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

አሁን ላይ ደግሞ ጎሕ ቤቶች ባንክ ልምድና ብቃት ባላቸው ሠራተኞቹ አማካኝነት በራስ አቅም በመታገዝ “ጎሕ ሞባይል አፕ” (Goh Mobile APP) የተሰኘ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ አበልጽጎ በዛሬው ዕለት ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ሥራ አስጀምሯል፡፡ ይህ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጀመሪያው ዙር የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ማከናወን ያስችላል፡፡

  • የሂሳብዎን ዝርዝር መግለጫ ለማስተዳደርና ለመከታተል ያስችላል፡፡
  • ከአንድ በላይ ሂሳብ ካልዎ በቀላሉ ለማስተዳደርና ለመከታተል ያስችላል፡፡
  • ከራስዎ የጎሕ ቤቶች ባንክ ሂሳብ ወደ ሌላ የጎሕ ቤቶች ባንክ ሂሳብ ወይም ቴሌብር ገንዘብ በቀላሉ ለማስተላለፍ ያስችላል፡፡
  •  ከራስዎ የጎሕ ቤቶች ባንክ ሂሳብ ወደ ሌላ ባንክ ሂሳብ ወይም ቴሌብር ገንዘብ በቀላሉ ለማስተላለፍ ያስችላል፡፡
  •  የአየር ሠዓት ለራስዎም ሆነ ለወዳጅ ዘመድዎ ከኢትዮ ቴሌኮም በቀላሉ ለመግዛት ያስችላል፡፡
  •  የዕየለቱን የውጭ ሀገር ገንዘቦች የምንዛሪ ተመን ለማወቅና ተመጣጣኝ የብር መጠንን ለማስላት ያግዛል፡፡

በአነስተኛ የኢንተርኔት ዳታ በላቀ ፍጥነት መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡ ይህ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ አዲሱን የአለም አቀፍ እና የኢንሳን መሰረታዊ የደህንነት መስፈርት ያሟላና ደህንነቱ የተረጋገጠና የተፈቀደ በመሆኑ ለደንበኞች የባንክ አገልግሎት በአስተማማኝ ደህንነት እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል፡፡ በቀጣይም ባንካችን ይህን የሞባይል መተግበሪያ ተጨማሪ የክፍያ መስጫ አማራጮችን በማካተት የሚሰጠውን አገልግሎት ለደንበኞች ይበልጥ ምቹ ቀላልና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማደረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ይሰራል፡፡

ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ

የትውልዱ ባንክ !