Goh Betoch Bank

Bank of the Generation!                              SWIFT CODE: GOBTETAA

ጎሕ ቤቶች ባንክ አዳማ ቅርንጫፉን አስመረቀ!

አዳማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም፤ ጎሕ ቤቶች ባንክ ስድስተኛ ቅርንጫፉን በአዳማ ከተማ በመክፈት ሙሉ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡

በዕለቱ የተለያዩ የመንግስት መ/ቤት ተወካዮች፣ የባንኩ የቦርድና የሥራ አመራር አባላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ቅርንጫፍ ሥራ ማስጀመር ሥነ-ስርዓቱ ተከናውኗል፡፡

ጎሕ ቤቶች ባንክ በዋነኝነት ለቤት መግዣ፣ መስሪያና ማደሻ የሚሆን ብድር ማቅረብ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ባንክ ሲሆን ደንበኞች በቀረባቸው የባንኩ ቅርንጫፎች በመቅረብ የቁጠባ ሒሳብ በመክፈት እስከ 30 ዓመት በሚከፈል ብድር የቤት ባለቤት መሆን የሚያስችላቸውን አገልግሎት ይዞ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የንግድ ባንኮች የሚሰሩትን የባንክ አገልግሎቶች ጎን ለጎን የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ባንኩ የአዳማ ቅርንጫፉን ጨምሮ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ (ቦሌ፣ ለቡ እና ሲኤምሲ) እንዲሁም በክልል ከተሞች ድሬ-ዳዋና ባህር ዳር በከፈታቸው ቅርንጫፎቹ የተሟላ የባንክ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡