Goh Betoch Bank

Bank of the Generation!                              SWIFT CODE: GOBTETAA

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የምርጫ ውጤት

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የምርጫ ውጤት

ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. ባከናወነው 2ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በተደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመጽደቁ ሂደት እንደተጠበቀ ሆኖ የእጩ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዝርዝር ካገኙት ድምጽ ጋር አስመራጭ ኮሚቴው ባሳወቀው መሰረት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ የምርጫው የድምፅ ቆጠራ የብሔራዊ ባንክ እና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተወካዮች በተገኙበት በዕለቱ ተካሂዷል፡፡

በውጤቱም መሰረት በሁሉም ባለአክሲዮኖች ከተመረጡት እጩዎች መካከል ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ከፍተኛ ውጤት ያመጡት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ብቻ ከተመረጡት ደግሞ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ከፍተኛ ዉጤት ያመጡት በድምሩ 9 አባላት ለቀጣይ ሦስት ተከታታይ አመታት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሆነው ተመርጠዋል። እነሱም፡-

1.    አቶ ጌታሁን ናና ጀንበር

2.    ወ/ሮ ፋሲካ ከበደ ተመሠለው

3.    አቶ ሰመረ አሰፋ በሻህ

4.    ሬዳዋ ሞተርስ ኢንዱስትሪ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር (ተወካይ) አቶ ታደሰ አድማሱ

5.    አቶ ዘመተ ሥዩም አራጋው

6.    አቶ ሳምሶን ተስፋዬ ማሞ

7.    ውብሸት ዠቅአለ መንገሻ (ዶ/ር)

8.    ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ (ተወካይ) አቶ ሽመልስ ገድለጊዮርጊስ

9.    አቶ በላቸው ሁሪሳ ዳዲ 

ቀሪዎቹ እንደቅደም ተከተላቸው በተጣባባቂነት ተይዘዋል፡፡

ዝርዝሩን ለማየት እባክዎ ይህን ሊንክ ይጫኑት፡፡