ጉዳዩ፡ በባንኩ የምስረታ ወቅት በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው ያልፈረሙ ባለአክሲዮኖችን ይመለከታል፡
በባንኩ ምስረታ ወቅት በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው ያልፈረሙ ባለአክሲዮኖችን በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው አስፈላጊዉን ማለትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያዘው መሰረት የባለአክሲዮንነት ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያሟሉ በተላለፈው ተደጋጋሚ ጥሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለአክሲዮኖች ወደባንካችን ቀርበው አስፈላጊውን ቅደመ ሁኔታ ማሟላት ችለዋል። ነገር ግን በተላለፈውም ጥሪ መሰረት እስካሁን ወደባንኩ ያልቀረቡና አስፈላጊውን የባለአክሲዮንነት ቅድመ ሁኔታ ያላሟሉ አክሲዮን ገዢዎች አሉ። በመሆኑም ቦሌ ጃፓን ኤንባሲ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል እንዲሁም በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በአስቸኳይ በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0116 68 72 52 ወይም 0116 68 75 85፣ በኢ-ሜይል፡ gohshareadministration@gohbetbank.com በመጠቀም አስፈላጊ ሰነዶች አሟልተው የባለአክሲዮንነት ፊርማ እንዲፈርሙ በድጋሚ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ.