Skip to main content

Goh Betoch Bank

የጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
mobilelogo

የጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ.

የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

በኢፌዲሪ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና 370 እንዲሁም በባንኩ የተሻሻለ የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 17 እና 18 መሠረት የጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘዉ ጎልፍ ክለብ ይካሄዳል። በመሆኑም የተከበራችሁ የባንኩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪዉን ያስተላልፋል።

  1. የባንኩ መረጃዎች
    • የባንኩ ስም፡- ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ.
    • የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፡- አ.አ. ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 2፣ የቤት ቁጥር አዲስ፤ድረ ገጽ፣ https://www.gohbetbank.com/
    • የባንኩ የምዝገባ ቁጥር፡- MT/AA/3/0052524/2013
    • የባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- ብር _2,176,368,000.00
    • የባንኩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡-  ብር  1,548,473,000.00
  2. የ5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
    • የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ፣
    • የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ፣
    • የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅና አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣
    • እ.ኤ.አ የ2025/2026 የዳይሬክተሮች ቦርድን አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
    • እ.ኤ.አ የ2025/2026 የውጭ ኦዲተሮችን አመታዊ የሂሳብ ሪፖርት ማዳመጥ፣
    • በተራ ቁጥር4 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ መወያየትና መወሰን፣
    • በተራ ቁጥር5 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ መወያየትና መወሰን፣
    • እ.ኤ.አ የ2025/2026 የሂሳብ ዘመን የተጣራ ትርፍ አመዳደብ እና አከፋፈል ላይ መወያየትና መወሰን፣
    • የውጭ ኦዲተሮችን የ2025/26 ተጨማሪ ክፍያ መወሰን፣
    • የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2025/2026 አመታዊ የሥራ ዋጋ እና የ2026/27 ወርሃዊ አበል መወሰን፣
    • የውጭ ኦዲተሮችን መሾም እና የሥራ ዋጋቸውን መወሰን፣
    • የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማከናወን፣
    • የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፡፡
  1. ማሳሳቢያ
    • በጉባኤዉ ላይ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ በተሰጠ የዉክልና ሰነድ (ተወካይ ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የተወካዩን ማንነት የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ በመያዝ) ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በባንኩ የተዘጋጀዉን የዉክልና ቅፅ ሞልታችሁ በመፈረም ተወካይ በመሾም በጉባኤው እንዲሳተፉ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
    • አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛዉም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ተወካይ ብቻ ነዉ፡፡ ሆኖም ሥራ ላይ ያለዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም የባንኩ ሠራተኛ የባለአክሲዮን ተወካይ ሆኖ ሊሾም የማይችል መሆኑን እናሳዉቃለን።
    • ለተጨማሪ መረጃ የባንኩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251-116687252 በስራ ሰአት በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ