Goh Betoch Bank

Bank of the Generation!                              SWIFT CODE: GOBTETAA

What is Mortgage?

የቤት ብድር (ሞርጌጅ) ምንድን ነው? ለጀማሪ የሚረዱ የብድር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች

የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን አንድ ኢትዮጵያዊ ማሳካት ከሚፈልጋቸው መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በሀገራችን በአሁኑ ሰዓት እራሱን ችሎ የቤት ብድር (ሞርጌጅ) አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛ ባንክ እንደመሆናችን የእርስዎን ህልም ለማሳካት ከጎንዎ እንደቀረብን ይሰማናል፡፡
የቤት ባለቤት ለመሆን ዝግጁነትና ተነሳሽነቱ ካለዎት እንግዲያውንስ ወደ ትክክለኛው ቦታ መጥተዋል፡፡ በዚህ ርዕስ የተለያዩ የብድር፣ የቤት ብድር (mortgage loan) ዓይነቶችን ፣ መሰረታዊ የቤት ግዥ ሂደቶችን እና ሌሎችንም ጨምሮ መሰረታዊ ጉዳዮችን እንሸፍናለን፡፡

የቤት ብድር (Mortgage Loan) ምንድን ነው?

በጥልቅ ወደ ርዕሱ ከመግባታችን በፊት ስለ የቤት ብድር ፅንሰ-ሀሳብ እናውራ፡፡ በመጀመሪያ “የቤት ብድር” የሚለው ቃል ምንድን ነው?

የሞርጌጅ ብድር ወይንም በአማርኛ አቻ ትርጉሙ የቤት ብድር ማለት በአበዳሪ የፋይናንስ ተቋም እና ተበዳሪ በሆነ ደንበኛ መካከል በሚደረግ ውል፣ ተበዳሪዉ ቤት ለመግዛት፣ ለመገንባት፣ ለማደስ ወይም ለማሻሻል ሲፈልግ ለዚሁ ወጪ መሸፈኛ ከአበዳሪዉ የሚወስድና መልሶ የሚከፍል ገንዘብ ነዉ፡፡    ተበዳሪው  ከአበዳሪው ተቋም ብድሩን ለማግኘት የተወሰነ ገንዘብ በባንክ ሒሣብ ማስቀመጥ ወይም መቆጠብ የሚጠበቅበት ሲሆን አበዳሪው ደግሞ ከቤት ጋር በተያያዘ ለተበዳሪው የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ገንዘብ  በብድር በማመቻቸት ተበዳሪዉ የቤት ባለቤት እንዲሆን የሚያመቻችበት ነው፡፡

የቤት ብድር ለማን ይሰጣል?

በዓለም አቀፍ ደረጃ አብዛኛው ማህበረሰብ ቤት ለመግዛት፣ ለማሻሻል ወይም ለመገንባት የቤት ብድር  ይጠቀማል፡፡እንዲኖርዎ የሚፈልጉትን ቤት ሙሉ ወጪ ከኪስዎ መሸፈን ካልቻሉ የቤት ብድር ከሚሰጡ ተቋማት ጎራ ማለት ተገቢ ነው፡፡

ቤት የሚገዙበት ገንዘብ በእጅዎ ቢኖርም በተለያዩ ምክንያቶች የቤት ብድርማግኘት የሚያስችልዎ አማራጮች ይኖርዎታል፡፡ ለምሳሌ፡- ባለሀብቶች አንዳንድ ጊዜ ንብረቶችን ለሌሎች ኢንቨስትመንቶች ገንዘብ እንዲያስለቅቅላቸው ለማድረግ የቤት ብድርን ይጠቀማሉ፡፡

በብድር እና በቤት ብድር(ሞርጌጅ) መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

“ብድር” የሚለው ቃል  ከፋይናንስ ግብይት ጋር በተያያዘ አበዳሪ የሆነ ወገን ተበዳሪ ለሆነ ወገን ገንዘብ ለመስጠት የሚስማማበት እና ተበዳሪዉ ደግሞ ገንዘቡን ተቀብሎ ከተጠቀመበት በኋላ መልሶ ለመክፈል የሚስማማበትን ሂደት ያሳያል፡፡

የቤት ብድር ከብድር ዓይነቶች መካከል አንዱ  ሲሆን በዋናኛነት ብድሩ የሚሰጠው ከማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የቤት ብድር የንብረት ዋስትና ያለዉ የብድር ዓይነት (Secured Loan)  ነው፡፡ የንብረት ዋስትና ያለዉን ብድር ተበዳሪው ለአበዳሪውበተለያዩ ምክንያቶች መልሶ መክፈል ቢያቅተው አበዳሪዉ የመያዣ ንብረቱን ላልተከፈለ ብድር ክፍያ የማዋል መብት ይኖረዋል፡፡ ይህ የመያዠ ንብረትን ላልተከፈለ ብድር ክፍያ የማዋል መብትን የማቋቋም ሒደት የመያዣ ምዝገባ ወይም በተለምዶ  እገዳ ተብሎ ይጠራል፡፡

የቤት ብድር (ሞርጌጅ) እንዴት ይሰራል?

የቤት ብድር ሲያገኙ፣ አበዳሪው ተቋም መበደር ለሚፈልጉት ንብረት ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ በብድር መልክ ያመቻችልዎታል፤ ለመክፈል ሲወስኑ ደግሞ በተበደሩት የገንዘብ መጠን ላይ ወለድ በማሰብ በረጅም ዓመታት እንዲከፍሉት ያደርጋል፡፡ አበዳሪው በንብረቱ ላይ ያለው የዋስትና መብት  ብድሩ አስቀድሞ በተደረገዉ ውል በተቀመጠዉ የአከፋፈል ሥርዓት መሠረት ሙሉ በሙሉ ተከፍሎ እስኪጠናቀቅ የሚቆይ ይሆናል፡፡

የብድር ክፍያ ከሌሎች ብድሮች የሚለየው አበዳሪዎ ብድር መክፈል ካልቻሉ የጠፋውን ኪሳራ ለመመለስ ንብረቱን ሊሸጥ ስለሚችል ነው። ያንን የክሬዲት ካርድ ሂሳብ ካልከፈሉ ከሚሆነው ጋር ያወዳድሩ፡ ምንም እንኳን ሂሳብዎን ወቅታዊ ለማድረግ እና በክሬዲት ነጥብዎ ላይ መጥፎ ተጽእኖዎችን ለመቋቋም ዘግይተው ቅጣት መክፈል ሊኖርብዎ ቢችልም የገዙትን እቃዎች መመለስ አይጠበቅብዎትም.

en_USEnglish