ለጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ በአስመራጭ ኮሚቴ አማካይነት እንዲከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ በባንኩ የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ መመረጡ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት ኮሚቴው የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላትን ጥቆማ ከግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 08 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ የሚቀበል ስለሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SSB/71/2019 እና SSB/79/2021 ላይ የተዘረዘሩ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩ የቦርድ አባላትን እንድትጠቁሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
- የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ/ች፤
- ዕድሜ 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
- የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ች፤
- በማንኛውም ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ/ች፤
- ሀቀኛ ታማኝ እና መልካም ዝና ያለው በተለይም በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆኑ የሒሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከስሶ በፍ/ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሠጥቶበት የማያውቅ/የማታውቅ፤
- በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ አባል ያልሆነ/ች፤
- በንግድ ሥራ አስተዳደር በተለይም በፋይናንስ ወይም በባንክ ስራ በቂ የስራ ልምድ ያለው/ላት ቢሆን ይመረጣል፤
- በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሳኔ ያልተሰጠበት/ባት፤
- በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያ ያልተወሰደበት/ባት፤
- የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሃራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም እሱ የሚመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት/ባት፤
- በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት/ባት፤
- ታክስ ባለመክፈል ተከስሶ ጥፋተኛ ያልተባለ/ች፤
- ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት እንዲሁም፤
- ሌሎች በሕግ የተገለፁ መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡–
- ጥቆማው ቦሌ መንገድ የቀድሞ ጃፓን ኢንባሲ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋና መ/ቤት 6ኛ ፎቅ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት፣ በባንኩ ቅርንጫፎች፣ በኢሜል አድራሻ BoDs.election@gohbetbank.com ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1704 ኮድ 1250 አ.አ “ለጎሕ ቤቶች ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት” በመላክ ማቅረብ ይቻላል፡፡
- ከነባር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትም መጠቆም ይቻላል፡፡
- ለዚሁ ተግባር በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች የተቀመጡ ቅፆችን ሞልቶ እና ፈርሞ ለቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ ወይም ለሚወክለው ሰው በማስረከብ ጥቆማ መስጠት ይቻላል፡፡
- በተጨማሪም ለባለአክሲዮኖች መጠቆሚያ የተዘጋጀውን ቅፅ ከባንኩ ዌብሳይት https://www.gohbetbank.com/ ወይም ቴሌግራም Gohbetochbank ማውረድ ወይም ከምልመላ እና ምርጫ ኮሚቴ ጊዜያዊ ፅ/ቤት በመውሰድ እና ቅፁን ሞልቶ በመፈረም መመለስ ይቻላል፡፡
- ነሀሴ 08 ቀን 2015 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ከወዲሁ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ጎሕ ቤቶች ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ